ትኤምኃክሙ ኅሪት ደብረ ገነት ቅዱስ አማኑኤል ወኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን እንተ ሀለወት በተዐይነ ዴልወር ካውንቲ ሞርተን ፔንስልቫንያ

በዴልወር ካውንቲ በሞርተን ከተማ በፔንስልቫንያ ግዛት የምትገኘውየተወደደችው ደብረ ገነት ቅዱስ አማኑኤል ወኪዳነ ምሕረትቤተ ክርስቲያን ሰላምታ ታቀርብላችኋለች

ደብረ ገነት ቅዱስ አማኑኤል ወኪዳነ ምሕረት ኢትዮጵያን ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን
Debre Genet Kidus Amanuel and Kidane Mihret
Ethiopian Orthodox Tewahedo Church
የቤተ ክርስቲያን ማንነታችን
Who We Are
- 
On August 31/1996, a prayer service was started with the blessing of (Liqe Liqawunt) Workneh Haile. From August 31/1996 to 2024, Debre Genet Kidus Amanuel We Kidane Mihret Church is the first Ethiopian Orthodox Tewahedo Church in the city of Philadelphia during the era of Chancellor Vanya.
 - 
From August 31/1996 to September 19/1999, it served at 43 and Chestnut in a rented church.
 - 
From September 19/1999, the 6825 Green Way Avenue building was purchased and the Archbishop, Abune Zena Markos, who was the assistant of His Holiness Abune Tekle Haimanaot and His Holiness Abune Merkoreos, blessed us with service until 2004.
 - 
On October 31/2004, His Holiness Abune Isaac, who was the archbishop of the western countries, blessed the renovated main church and it is still providing services to the believers until November 18/2018. After the debt was settled and an audit was requested, the board members decided to close the church, arguing that the audit was unnecessary. For four consecutive weeks, despite our repeated requests to reopen the church, they were unable to do so.
 - 
Our ark, Amanuel and our name Debre Genet, was rented from the Indian Orthodox Tewahedo Church located at 4400 State Road, Drexel Hill, Delaware County, and was blessed by the archbishop of the diocese at the time.
 - 
Adding Kidane Mihret ark, our church has been providing services at the Indian Orthodox Tewahedo Church until January 7/2020.
 - 
Since January 7/2020, we have purchased a church in Morton City, Delaware County, Pennsylvania State 14-16 South Morton Building and are providing services.
 - 
Debre Genet Kidus Amanuel We'Kidane Mihret Ehtiopian Orthodox Tewahedo Church Parish Spiritual Management Assembly is the responsible party.
 
•ኦገስት 31/1996 በሊቀ ሊቃውንት ወርቅነህ ኃይሌ ተባርኮ ጸሎተ ቅዳሴ ተጀመረ። ከኦገስት(Aug) 31/1996 እስከ 2024 ደብረ ገነት ቅዱስ አማኑኤል ወኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን በፊላደልፊያ ከተማ በፔንስልቫንያ ክፍለ ሀገር የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ነው
 
•በኦክቶበር (October )31/2004 የምዕራብ አገሮች ሊቀ ጳጳስ የነበሩት ብፁዕ አቡነ ይስሐቅ የታደሰውን ዋና ቤተ ክርስቲያን ተባርኮ እስከ ኖቨምበር 18/2018 ድረስ ለምእመናን አገልግሎት በመስጠት ላይ እንዳለ የቤተ ክርስቲያኑ ዕዳ ተከፍሎ እንዳበቃ ኦዲት (የሂሳብ ምርመራ ) እንዲደረግ ተጠይቆ ሳለ በወቅቱ የነበሩ የቦርድ አባላት ኦዲት መደረግ የለበትም በማለት ቤተ ክርስቲያኑን ዘጉት ለአራት(4) ተከታታይ ሳምንት ተመላልሰን እንዲከፍቱልን ብንጠይቅ ሊከፍቱልን አልቻሉም
•ከAug 31/1996 እስከ ሴብቴምበር (September)19/1999 ድረስ 43 እና ቼስተነት(Chestnut) በኪራይ ቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ሰጥቶአል
•ከሴብቴምበር (September) 19/1999 ጀምሮ 6825 ግሪን ወይ አቬኑ ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ተገዝቶ የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ተክለ ሃይማኖትና የብፁዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ ረዳት (እንደራሴ )የነበሩት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ዜና ማርቆስ መቃኞውን ባርከውልን እስከ 2004 አገልግሎት በመስጠት ቆይቶአል
ታቦታችን አማኑኤልንና ስማችንን ደብረ ገነትን ይዘን ወደ ዴልዋር ካውንቲ ድሬክሴል ሂል 4400 ስቴት ሮድ ላይ በሚገኘው የሕንድ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተከራይተን በወቅቱ በነበሩት የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ ተባርኮ ጃንዋሪ 7/2019 የልደት ዕለት አገልግሎቱ ቀጠለ
የቅድስት ኪዳነ ምሕረትን ታቦት በመደረብ እስከ ጃንዋሪ 7/2020 ድረስ በሕንድ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ኪራይ አገልግሎት ሲሰጥ ቆይቶአል
 
•ከጃንዋሪ 7/2020- ጀምሮ በዴልዋር ካውንቲ በሞርተን ከተማ በፔንስልቫንያ ክፍለ ሀገር 14- 16 ደቡብ (South) ሞርተን ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ገዝተን አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል
የደብረ ገነት ቅዲስ አማኑኤል ወኪዳነ ምሕረት ቤተ ክርስቲያን ሰበካ መንፈሳዊ አስተዳደር ጉባኤ
